
ባሕር ዳር: ጥር 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት “ያለንበት ሁኔታ እጅግ ተለዋዋጭ ውስብስብ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካልና ኢኮኖሚ ችግሮች ያሉበት ግን ደግሞ በሕብረት መቆም እስከቻልን ድረስ አቅማችን ከችግሮቻችን በላይ ማድረግ እንችላለን” ብለዋል፡፡
አንድነት ኀይል ነው፤ ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን ትተን በሙሉ አቅማችን ለጋራ ዓላማችን ስኬት እንሥራ ያሉት ኃላፊው ለእውነተኛ ወንድማማችነት እና አንድነት ሁሉን አቀፍ ትግል ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ከችግር መውጫ ቁልፉ መንገዱ በችግሮች ላይ የጋራ አረዳድ መፍጠር፣ አቅምን ማሰባሰብና ለጋራ ጉዳዮቻችን በቅንጅት መስራት ነው ብለዋል፡፡
የተበተነ አቅም ከጥቅሙ ኪሳራው እንደሚያመዝን የገለጹት አቶ ይርጋ ጠንካራ አንድነት መፍጠርና የችግር መፈልፈያ በሮችን በመዝጋት ለዓላማችን ስኬት ከፍ ያለ ድርሻ ባላቸው ተግባራት ላይ እንድናተኩር ያግዘናልና በአንድነት እንትጋ ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!