
አዲስ አበባ: ጥር 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በገቢዎች ሚኒስቴር የመከካለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለታማኝ ግብር ከፋዮች ዕውቅና እየሰጠ ነው። ግብራቸውን በታማኝነት የከፈሉ 127 መካከለኛ ግብር ከፋዮች የታማኝነት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሰብለ ሀጎስ ለግብር ከፋዮች ዕውቅና ለመስጠት 70 በመቶ ሕግ እና ሥርዓትን አክብሮ መሥራት እና 30 በመቶ ደግሞ የሰበሰቡት የገቢ መጠን እንደመስፈርት መወሰዱን ተናግረዋል።
ይህ መርሐ ግብር በዋናነት ሕጋዊ አሠራርን በማበረታታት ሁሉም ግብር ከፋዮች በታማኝነት ግብር እንዲከፍሉ ለማስቻል ነው ብለዋል ሥራ አሥኪያጇ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!