የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች በገበታ ለትውልድ የሚለማዉን ሎጎ ሐይቅ እየተመለከቱ ነው።

15

ደሴ: ጥር 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች በገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የሚለማውን ሎጎ ሐይቅ እየተመለከቱ ነው።

ሎጎ ሐይቅ በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኝ ለዕይታ ማራኪ ቦታ ሲኾን የቱሪስት መስህብነቱን የበለጠ ለማሳደግ በገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ታቅፎ የማልማት ሂደቱ ተጀምሯል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሴቶች የክልሉ ሰላም እንዲረጋገጥ እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ።
Next articleበገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለ127 መካከለኛ ግብር ከፋዮች የታማኝነት ዕውቅና ሰጠ።