በምዕራብ ጎንደር እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞን አጎራባች ወረዳዎች የሚገኙ የተለያዩ የኀብረተሰብ ክፍሎች በወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ እየመከሩ ነወ።

19

ባሕር ዳር: ጥር 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞን አጎራባች ወረዳዎች የሚገኙ የተለያዩ የኀብረተሰብ ክፍሎች በወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ በምዕራብ ጎንደር ዞን አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ነጋዴ ባሕር ከተማ ነው እየመከሩ የሚገኙት።

በምክክሩ የሁለቱም ዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጄኔራሎች፣ የአዳኝ አገር ጫቆ እና የጭልጋ ወረዳ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሃይማኖት አባቶች እና ወጣቶች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበባዮ ኢነርጂ ዘርፍ ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገቡ የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ዕውቅና አገኘ።
Next article“ኢትዮጵያ የባሕር በር የመፈለጓ መሰረታዊ መነሻ የህልውና ጉዳይ ነው” የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ