በተሁለደሬ ወረዳ እና በሐይቅ ከተማ በየደረጃው ለሚገኙ የጸጥታ አካላት የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።

18

ደሴ: ጥር 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን በተሁለደሬ ወረዳ እና ሐይቅ ከተማ በየደረጃው ለሚገኙ የጸጥታ አካላት “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልእክት የአቅም ማጎልበቻ ንድፈ ሀሳባዊ እና ግምገማዊ ሥልጠና ተሰጥቷል።

የደቡብ ወሎ ዞን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኀላፊ እያሱ ዮሐንስ በመድረኩ ዓለማቀፋዊ፣ ሀገራዊ፣ ክልላዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ በክልል ደረጃ የተዘጋጀውን ሰነድ ለሠልጣኞቹ አቅርበዋል።

በዚህም ተሳታፊዎቹ እነዚህን ነባራዊ እውነታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ወቅቱ የሚጠይቀውን ዝግጅት ማድረግ ይገባቸዋልም ተብሏል።

የፓለቲካ አመራሩ የክልሉን የጸጥታ ችግር ለመፍታት የመልካም አሥተዳደር፣ የልማት እና የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን በአግባቡ መፍታት እንዳለበት በመድረኩ ተነስቷል።

የሥልጠናው ተሳታፊ ረዳት ኢንስፔክተር ሰብለ ጎንፋ እና አደም ኢብራሂም ሥልጠናው ወቅታዊ ሁኔታዎችን የተገነዘቡበት እና የጸጥታ ሥራቸውን በውጤታማነት ለመፈጸም አቅም የሚፈጥሩበት እንደኾነ ተናግረዋል።

ሥልጠናው ለተከታታይ አምስት ቀናት እንደሚሰጥ የወጣው መረሐግብር ያመለክታል።

ዘጋቢ፦ አንተነህ ፀጋዬ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከመንግሥት ጋር ተባብረው ድርቅ ያስከተለውን ችግር ለመቅረፍ ሊያግዙ ይገባል” ዶክተር ድረስ ሳህሉ
Next articleበባዮ ኢነርጂ ዘርፍ ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገቡ የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ዕውቅና አገኘ።