
ደሴ: ጥር 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኮምቦልቻ ከተማ የተሠሩ የልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል።
በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) ጨምሮ የክልልና የዞን የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በከተማዋ ከሚመረቁ ፕሮጀክቶች መካከል የኮምቦልቻ መናኸሪያ፣ ትምህርት ቤት እና የተለያዩ የኢንቨስትመንት ልማቶች ይገኙበታል።
በተመሥገን አሰፋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!