
ባሕር ዳር: ጥር 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢምባሲዎች አድማሱ እና አውዱ የሰፋ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።
አቶ ደመቀ ዛሬ በተጠናቀቀው ዓመታዊ የአምባሳደሮች ጉባኤ ላይ የሥራ መመሪያ በሰጡበት ወቅት እንዳሉት የሚሲዮኖችን አድማስ ከፍ በማድረግ የኢትዮጵያን ተፈላጊነት፣ ተደራሽነት እና ተደማጭነት እንዲጨምር ለማድረግ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
ከሀገሮች ጋር ያለን የሁለትዮሽ ግንኘነት እንዲጠናከር እና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲያችን እንዲሰፋ በማድረግ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ማረጋገጥ ይገባል ማለታቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!