ባለፉት ስድስት ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አገልግሎቶች ተሠጥቷል፡፡

16

ባሕር ዳር: ጥር 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ባለፉት ስድስት ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ 1 ሚሊዮን 545 ሺህ 514 የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አገልግሎቶች (በኦን ላይን እና በባክ ኦፊስ) መሰጠቱን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። አፈጻጸሙ ከግማሽ ዓመት እቅድ አንፃር ሲታይ 73 ነጥብ 6 በመቶ ነው ተብሏል። የተሠጡት አገልግሎቶች አዲስ የንግድ ምዝገባ፣ አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ፈቃድ እድሳት፣ ማሻሻያ፣ የንግድ ሥም እንዲሁም መሠል 19 የተለያዩ አገልግሎቶችን ያካተተ ነው፡፡

በፌደራል ደረጃ ባለፉት ስድስት ወራት ከ93 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አገልግሎቶች በኦን ላይን የተሠጡ ሲሆን በእድሳት ወቅት ቅዳሜ እና እሑድን ጨምሮ በእረፍት ቀናት አገልግሎት መሠጠቱ ለዘርፉ የተሻለ አፈፃፀም መገኘት ምክንያት መኾኑ ተጠቅሷል፡፡ በ2016 በበጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አገልግሎቶችን ለመስጠት መታቀዱን ከንግድና ቀጣናዊ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል ያጋጠመውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት የምሁራን ሚና ከፍተኛ መኾኑ ተገለጸ።
Next article“ኢምባሲዎች አድማሱ እና አውዱ የሰፋ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል” አቶ ደመቀ መኮንን