
ደሴ: ጥር 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የምሁራን ሚና በሚል ርዕስ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ከምሥራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት ጋር በደሴ ከተማ ውይይት እያደረጉ ነው። በመድረኩ ከወሎ፣ ከወልዲያ እና ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን እየተሳተፉ ነው።
የምሥራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት ሠብሣቢ እና የሰሜን ምሥራቅ እዝ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮለ ለሀገር ዘላቂ ሰላም የምሁራን ሚና ከፍተኛ መኾኑን ገልጸዋል። ውይይቱ በአማራ ክልል ያሉ የጸጥታ ችግሮችን በማስወገድ ምሁራን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ያለመ እንደኾነ ጠቅሰዋል።
የጋራ መግባባት በመፍጠር መሥራት እንደሚገባም ሌተናል ጄኔራሉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ ተመሥገን አሰፋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!