“አርብቶ አደሮችን የኢኮኖሚ ብቻ ሳይኾን የደኅንነት መሠረት አድርገን ልንጠቀም ይገባል” ታገሰ ጫፎ።

26

ባሕርዳር: ጥር 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የምስራቅ አፍሪካ የአርብቶ አደሮች ኤክስፖ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፍቷል።

በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ “የምግብ ዋስትና እና የድርቅ ችግሮች አሉብን፤ ይህንን ችግር ለመፍታት ቀጣናዊ ትስስር እና ልማትን ማሳደግ ያስፈልጋል” ብለዋል።

“ለርሃብ የተጋለጥነው የሀብት ችግር ስላለብን አይደለም። በአንድ የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢ ብንመለከት ከብት በበረት አንጂ በቁጥር አይለካም፤ ስለዚህም መግባባትን በማሳደግ የግጦሽ መሬት መሸርሸርን በመቀነስ ትልቅ የኢኮኖሚ ግብአት ማድረግ ይገባል። የኢኮኖሚ አድገትን ማሳደግ ብቻ ሳይኾን የደኅንነት ምንጭ ማድረግ ይገባናል” ነው ያሉት።

በመኾኑም የምስራቅ አፍሪካ ጎረቤታም ሀገሮች ወንድማማችነት አሳድገን በጋራ አልምተን እና ቤተሰባዊነታችን አሳድገን ችግራችንን ልንቀርፍ ይገባል ነው ያሉት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለስደተኞች ማኅበራዊ ጥበቃ በዲጂታል መንገድ ትምህርት እና ሥልጠና እንዲያገኙ እየተሠራ መኾኑን ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት ገለፀ።
Next article“ዛሬ በአማን ጊዜ ፈረሱን ለእርቅ እና ለሰላም እየተጠቀምንበት ነው” የአገው ፈረሰኞች ማኅበር