
ባሕርዳር: ጥር 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ድርጅቱ 11 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የዲጂታል ዘርፉን በመደገፍ ለወጣቶች እና ሴቶች የሥራ እድል ለመፍጠር ያለመ የሦስትዮሽ ስምምነት ተፈራርሟል።
ድርጅቱ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአይቲ ፓርክ ኮርፖሬሽን እና ከሶማሌ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ነው በዛሬው እለት የተፈራረመው።
በስምምነቱ መሠረት የአይቲ ፓርክ ኮርፖሬሽን ከተለያዩ ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶች በፓርኩ ውስጥ ራሳቸውን እንዲያበቁ የሚሠራ ይኾናል።
በሶማሌ ክልል ያሉ ስደተኞች የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲኾኑ እና ለወጣቶች የተሰጥኦ ማእከላት አስፈላጊ ግብአቶችን የሚያሟላ ይኾናል ተብሏል።
ድርጅቱ በሚቀጥሉት ዓመታት በሁሉም ክልሎች ለሚገኙ ስደተኞች የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽ እንዲኾን እንደሚሠራም ተገልጿል።
ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!