
ባሕር ዳር: ጥር 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢኮኖሚ ዕድገቱ ከዚህ በላይ ለመሄድ እንዳይችል አንዱ ዕንቅፋት በጠባብ ቡድናዊ ፍላጎት የተፈጠሩ ትሥሥሮች ያስከተሏቸው አካባቢያዊ ግጭቶች መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በስብሰባው ገምግሟል።
እነዚህን ግጭቶች በመፍታት የብልፅግና ጉዞን ይበልጥ ለማፋጠንና የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሚያስችል አግባብ የተሟላ ሀገራዊ ሰላም ለማስፈን እንዲቻል ከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በስብሰባው አቅጣጫ ተቀምጧል።
በሰላማዊ የፖለቲካ መንገድ ጥያቄዎቻቸውን ለሚያቀርቡ አካላት ሰላማዊ መንገዶች እስከሚቻለው ድረስ እንዲመቻቹ፤ ዓላማቸው በነፍጥ ፍላጎታቸውን ማስፈጸም በሆኑ አካላት ላይ ደግሞ፣ ተገቢው ሕግን የማስከበር ሥራ በተጠናከረ መንገድ እንዲካሄድም ውሳኔ ተላልፏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
