የባሕር በር ለማግኘት የተፈረመውን የመግባቢያ ሥምምነት ወደ ተግባራዊ ሥምምነት ለማድረስ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ አሳለፈ።

26

ባሕር ዳር: ጥር 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ከሶማሌ ላንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባራዊ ስምምነት ለማድረስ፣ ከሌሎች ጎረቤት ሀገራትም ጋር ተጨማሪ የባሕር በር አማራጮችን በሰጥቶ መቀበል መርሕ ለማግኘት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ አሳልፏል።

ኢትዮጵያ እያደገ ከሚሄደው የሕዝብ ብዛቷና ኢኮኖሚዋ ጋር የሚመጣጠን የባሕር በር እንደሚያስፈልጋት ፓርቲው ካስቀመጠው አቅጣጫ በመነሣት፣ የተከናወኑ ተግባራት የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ቀናት ባደረገው ስብሰባ ተገምግመዋል።

በዚህም ከሶማሌ ላንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ የኢኮኖሚና የባህል ትሥሥር ያላትን አቋም የሚያሳይ መሆኑ ታይቷል።

በቀጣይም የተጀመረውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባራዊ ስምምነት ለማድረስ፣ ከሌሎች ጎረቤት ሀገራትም ጋር ተጨማሪ የባሕር በር አማራጮችን በሰጥቶ መቀበል መርሕ ለማግኘት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሠራ ውሳኔ ተላልፏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መግለጫ አውጥቷል።
Next articleከታጣቂ ቡድኖች ጋር የተጀመሩ ሰላማዊ አማራጮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቅጣጫ አስቀመጠ።