በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የታየውን አንጻራዊ ሰላም ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።

13

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የታየውን አንጻራዊ ሰላም ማስቀጠል እንደሚገባ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ አፈ ጉባኤ ፋንታይቱ ካሴ ገለጹ።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 26ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የብሔረሰብ አሥተዳደሩ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፈንታይቱ ካሴ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የታየውን አንጻራዊ ሰላም ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።

አፈ ጉባኤዋ በዋግ ኽምራ በ2015/16 የምርት ዘመን በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ያደረጉ ድርጅቶችን፣ የመንግሥት ተቋማትን፣ ግለሰቦችን እና ማኅበራትን በብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት ሥም አመስግነዋል።

በቀጣይም የእንሰሳት እና የሰው ሕይዎትን ከመጥፋት ለመታደግ የሰብዓዊ ድጋፎች እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ:- ደጀን ታምሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleባሕርዳር ከተማ ከንግድ ባንክ ተጠባቂው የፕሪሜየር ሊግ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።
Next articleአቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን በአብላጫ ድምጽ ተመረጡ።