
ሰቆጣ: ጥር 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 26ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው የሁለት ቀናት ቆይታ የተለያዩ ጉዳዮች ተነስተው ይመከርባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። በመጀመሪያ ቀኑ የምክር ቤቱ ስብሰባ የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የበጀት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ይገመገማል።
ምክር ቤቱ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትም አድምጦ ይገመግማል ተብሏል።
ጉባኤው ነገ ጥር 18/2016 ዓ.ም በሚኖረው ውሎም ከምክር ቤት አባላት የተነሡ ጥያቄዎችን በማዳመጥ ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጥባቸው ይጠበቃል። በጉባኤው መዝጊያ ላይ ምክር ቤቱ ያስገነባው ባለ ሦስት ወለል ሕንፃ ተመርቆ ለሥራ ክፍት እንደሚኾን መርሐ ግብሩ ያመላክታል።
ዘጋቢ:- ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!