ምሁራን ሀገራዊ መግባባት ላይ እንዲደረስ ሚናቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አሳሰበ።

36

አዲስ አበባ: ጥር 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገራዊ ምክክሩ የምሁራንን ሚና በተመለከተ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር መክሯል።

እንደ ሀገር ያሉትን አለመግባባቶች በምክክር ለመፍታት የተቋቋመው ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን በሕዝቡ እና አጋር አካላት ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው አካታች ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረ ስላሴ ገልጸዋል።

ምሁራን ያላቸውን እውቀት እና ያካበቱትን ልምድ ተጠቅመው ሀገራዊ መግባባት ላይ እንዲደረስ አስተዋጽኦ በማበርከት ተሳትፎ እንዲያደርጉም ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ አሳስበዋል።

ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት የምሁራን ሚና፣ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎች እና የምክክሩ ተስፋ እና ስጋትን የተመለከቱ የመነሻ ጹሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል።

ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች መንግሥት አፋጣኝ ሰብአዊ እርዳታ እያደረሰ ነው” የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት
Next articleትር 15/2016 ም.አ ቺርቤዋ ጋዚቲ