
አዲስ አበባ: ጥር 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ዛሬ በሰጠው መግለጫ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔን በስኬት ለማስተናገድ በቂ ዘግጅት መደረጉን አስታውቋል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሀገሪቱ ሰሞኑን የተከበሩት የገና እና የጥምቀት በዓላት በድምቀት እና በሰላም መጠናቀዋቸውን ገልጸዋል። የሕዝቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ተባብሮ መሥራት ወሳኝ ሚና እንደነበረው ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔን እንደምታስተናግድ በመግለጽ፤ ለመስተንግዶው መንግሥት የበኩሉን ዝግጅት ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡
ጉባዔው በሰላም እና በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን የጠቀሱት ሚኒስትር ድኤታዋ ኅብረተሰቡም ከፀጥታ አካላት ጋር መተባባር የአካባቢውን ሰላም ማስጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡
ጉባዔው የሀገሪቱ ገጽታ እና የዲፕሎማሲ ስኬት የሚገለጽበት በመኾኑ ለስኬታማነቱ ሁሉም ወገን የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፦ ቤቴል መኮንን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!