የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ገለጸ።

16

ባሕር ዳር፡ ጥር 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬው እለት ውይይት በማድረግ ላይ ነው።

ኮሚቴው ሀገራዊ፣ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥ ይሆናል።

ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ አንድምታ ያላቸው ይዘቶች በመርሀግብሩ ላይ በአግባቡ የሚመከርባቸው ሲሆን እንደ ሀገር በብሔራዊነት ትርክት የጀመርነውን ጉዞ ማጠናከር የሚችሉ ግብአቶች እንደሚገኙበት ይጠበቃል።

ውይይቱ በቀጣይ ቀናትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ገለፃዎች እና የቡድን ውይይቶች የመርሀ ግብሩ አካል ናቸው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ሕዝብ ለባሕል እና እሴቶቹ ዳብረው መቀጠል የሚያደርገውን አበርክቶ አጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ጠየቀ፡፡
Next articleበተፋሰስ ልማት ሥራዎች የአፈር እርጥበትን መጠበቅ በመቻሉ ምርታማ መኾናቸውን አርሶ አደሮች ተናገሩ።