53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከጥር 21 እስከ 26 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ይካሄዳል።

31

ባሕር ዳር: ጥር 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከ1963 ዓ.ም ጀምሮ መካሄድ በጀመረው እና በኢትዮጵያ አትሌቲክስ የውድድር ታሪክ አንጋፋ በኾነው የዘንድሮው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከተለያዩ ክልሎች፣ ክለቦች እና ተቋማት የተውጣጡ 1ሺህ 102 አትሌቶችም ይሳተፋሉ።

ከዚህ ውድድር የተመረጡ አትሌቶች በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ሀገርን ይወክላሉ።

እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ለሚሳተፉ አትሌቶችም አቅማቸውን በውድድሩ ለመፈተሽ የሚያግዝ ነው ተብሏል።

ፌዴሬሽኑ ለዚህ ውድድር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።

ዘጋቢ፡- ባዘዘው መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለውጭ ሀገራት ከተሸጠ ኃይል ከ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
Next articleየአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለ84ኛ ጊዜ ለሚከበረው የአገው ፈረሰኞች በዓል እንግዶች እንዲታደሙ ጥሪ አቀረበ።