“ለውጭ ሀገራት ከተሸጠ ኃይል ከ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

22

ባሕር ዳር: ጥር 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ከቀረበ የኃይል ሽያጭ 12 ቢሊየን 848 ሚሊየን 139 ሺህ 990 ብር መገኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

ከኃይል ሽያጭ 13 ቢሊዮን 473 ሚሊየን 246 ሺህ 943 ብር ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር ተገልጿል። ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ 10 ቢሊዮን 234 ሚሊየን 869 ሺህ 88 እንዲሁም ለውጭ ሀገራት ከተሸጠ ኃይል 2 ቢሊዮን 613 ሚሊየን 270 ሺህ 902 ብር መገኘቱ ተጠቅሷል፡፡

ከኢትዮጵያ የኃይል ምርቱን የገዙ የውጭ ሀገራትም÷ ጅቡቲ፣ ሱዳን እና ኬንያ መኾናቸው ተብራርቷል፡፡ የግማሽ ዓመቱ አፈጻጸምም 95 ነጥብ 36 በመቶ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ገልጸዋል፡፡

በግማሽ ዓመቱ ለማምረት የታቀደው ኃይል 10 ሺህ 788 ጊጋ ዋት ሰዓት መሆኑን እና 9 ሺህ 549 ነጥብ 2 ጊጋ ዋት ሰዓት ማምረት መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በኃይል የ1 ሺህ 317 ነጥብ 5 ጊጋ ዋት ሰዓት ወይም የ13 ነጥብ 79 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ነው የገለጹት፡፡

እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ ለመሸጥ የታቀደው 8 ሺህ 505 ጊጋ ዋት ሰዓት መሆኑን አስታውሰዋል። 7 ሺህ 788 ጊጋ ዋት ሰዓት መሸጡንም አረጋግጠዋል፡፡

አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ8 ነጥብ 5 በመቶ ዕድገት አለው ነው ያሉት፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየስዕል ጥበብ ተማሪዎች ከጦርነት ሥነልቦና እንዲወጡ እንደሚያግዝ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስ ኤድ ገለጸ።
Next article53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከጥር 21 እስከ 26 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ይካሄዳል።