
ደሴ: ጥር 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከ130 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ ትምህርት ቤት ገንብቶ አስመርቋል፡፡
በከተማው የተገነቡት ትምህርት ቤቶች ስድስት ሲኾኑ ከፌዴራል እና ከክልሉ መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተገነቡም ናቸው፡፡
የትምህርት ቤቶቹ መገንባት ከዚህ ቀደም የነበረባቸውን ችግር እንደሚያቃልልላቸው እና በዚህም ደስተኛ መኾናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወንድወሰን ልሳነወርቅ በትምህርት ቤቶቹ ግንባታ ወቅት የማኅበረሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር አስረድተዋል፡፡
የትምህርት ግብዓቶችን ከማሟላት አኳያ ከተማ አሥተዳደሩ ቁርጠኛ አቋም ይዞ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ፊኒክስ ኃየሎም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!