
ደብረ ብርሃን: ጥር 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ)መምሪያው በዘንድሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ 620 ሄክታር የሚጠጋ መሬት በልዩ ልዩ አካላዊ የአፈር እና ውኃ እቀባ ሥራ እንደሚሠራ ነው የገለጸው፡፡
በበጋው ወራት የተሠራውን የተፋሰስ ልማት ሥራ በክረምቱ ወራት በሥነ ሕይወታዊ ዘዴ ለማጠናከር 5 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ከ 7 ሚሊዮን በላይ ችግኝ የማፍላት ሥራ ይከናወናልም ብሏል፡፡
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ መርሻ አይሳነው በተፋሰስ ልማቱ ከ14 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉም አብራርተዋል፡፡
መምሪያው ዛሬ የተፈጥሮ ሃብት ልማት የንቅናቄ መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ አካሂዷል፡፡
ዘጋቢ፡- ፋንታነሽ መሐመድ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!