
ባሕር ዳር: ጥር 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በባለሥልጣኑ የእቅድ፣ በጀት ዝግጅት፣ ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክተር መሳፍንት አሞኜ እንደገለጹት 770 ሺህ 638 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ዩኒየኖች መካዘን ገብቷል። በዩኒየኖች በኩልም ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ ይገኛል ብለዋል።
የመርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ኀብረት ሥራ ማኀበር ዩኒየን ሥራ አሥኪያጅ ጌታቸው እሸቱ እንዳሉት ለመስኖ እርሻ የሚውል 60ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ እያሰራጨን እንገኛለን ነው ያሉት።
ዋና ሥራ አሥኪያጁ 1ሺህ 218 ኩንታል የእንስሳት መኖ አምርተው ለአርሶ አደሩ ማሰራጨታቸውንም ተናግረዋል።
ባለሥልጣኑ የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የእቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫ ግምገማን በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
ዘጋቢ፡- ሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!