
ባሕር ዳር: ጥር 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮ ቴሌኮም በ6 ወር የሥራ አፈጻጸም 42 ነጥብ 86 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱም ገልጿል። ኢትዮ ቴሌኮም የ2016 አም የበጀት አመት የመጀመሪያ መንፈቅ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርቧል።
በሪፖርቱም በ6 ወር ዉስጥ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን የተናገሩት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ የደንበኞች ብዛት 74 ነጥብ 6ሚሊዮን ማድረስ ተችሏል ነው ያሉት።
በግማሽ ዓመቱ በተደረጉ የኔትወርክ ማስፋፊያ በ3G በ4G በ5G በአጠቃላይ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ተጨማሩ ደንበኛ የሚያሰተናግድ አቅም መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በ6 ወር የሥራ አፈጻጸም ከ42 ነጥብ 86 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱም ተገልጿል።
በራሔል ደምሰው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!