
ባሕር ዳር: ጥር 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ኀላፊ ለማ ያደቻ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ ተቀብለው በመምጣት ላይ ለሚገኙ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከ15 እስከ 20 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል።
ለሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን በትኬትና በስካይላይት ሆቴል አገልግሎት ከ15 እስከ 20 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል ያሉት ኀላፊው ለእንግዶች በተሻለ ዋጋ የጉብኝት መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
በተጨማሪም በአዲስ አበባ በሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ ከ100 በላይ ለሚኾኑ እንግዶች ለአንድ ቀን ነጻ የጉብኝት ፕሮግራም መዘጋጀቱንም ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) ለሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!