ጋዜጠኛ እና ደራሲ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

20

ባሕር ዳር: ጥር 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አንጋፋው ጋዜጠኛ እና ደራሲ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) በአደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ሕይወቱ አልፏል።

በ1957 ዓ.ም በይርጋለም የተወለደው ጋዜጠኛ ገነነ፤ በኢትዮጵያ በእግር ኳስ ተጫዋችነት፣ በጋዜጠኝነት እና በመጻሕፍት ደራሲነት ይታወቃል።

ከ30 ዓመታት በላይ በስፖርት ጋዜጠኝነት ያሳለፈው ገነነ መኩሪያ፤ ፍትሃዊ የጠጅ ክፍፍል፣ መኩሪያ፣ ኢህአፓ እና የስፖርት መጻሕፍትን ለንባብ አብቅቷል።

ገነነ መኩሪያ በአሻም ቲቪ ትኩረታቸውን በስፖርት እና በታሪክ ላይ ያደረጉ “የገነነ” እና “ጥቁር እንግዳ” የተሰኙ ፕሮግራሞችን ለዓመታት በአዘጋጅነት እና አቅራቢነት ሲሠራ መቆየቱም ይታወቃል።

ለእግር ኳስ ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦም፤ በ2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተሰናዳው የካፍ ኮንግረስ ላይ የረጅም ዘመን አገልግሎት ሜዳይ እንደተበረከተለት ኢቢሲ ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ዓድዋን ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ሀገራዊ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
Next article“ለሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከ15 እስከ 20 በመቶ ቅናሽ አድርገናል” የኢትዮጵያ አየር መንገድ