
ባሕር ዳር: ጥር 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ዓድዋን ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ሀገራዊ የምክክር መድረክ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።
ሰላም ሚኒስቴር ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሀገራዊ የምክክር በመድረኩ “ዓድዋን ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታና ሀገራዊ እሴቶች” በሚል መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።
በመድረኩ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ.ር) ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መሐመድ ዑስማን(ዶ.ር)፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት፣ ምሁራን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
የምክክር መድረኩ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሰላምና ሀገር ግንባታ ፎረም እስከ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ‹”ዓድዋን ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ሀገር አቀፍ የንቅናቄ መድረክ አካል መኾኑም ተገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!