
ደሴ: ጥር 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 38ኛ መደበኛ ጉባኤ የድርጊት መርሐ ግብር በደሴ ከተማ አሥተዳደር እያካሄደ ይገኛል።
ጉባኤውን የሃይማኖት አባቶች መርቀው የከፈቱ ሲኾን የደሴ ከተማ አሥተዳደር አፈጉባኤ አሕመድ ሙህዬ ጉባኤውን በተመለከተ መነሻ ሃሳቦችን አቅርበዋል።
ምክር ቤቱ የ37ኛውን መደበኛ ጉባኤ ቃለጉባኤ መርምሮም አጽድቋል፡፡ የደሴ ከተማ አሥተዳደር የ2016 የልማት እና የመልካም አሥተዳደር የ2ኛ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማቅረብም በሪፖርቱ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
ጉባኤው ነገም ሲቀጥል የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የ2016 በጀት ዓመት የ2ኛው ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማቅረብ ውይይት ይደረጋል ነው የተባለው፡፡
ምክር ቤቱ የደሴ ከተማ አሥተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ መምሪያ የውስጥ ኦዲት የሥራ ሂደት የ2016 በጀት ዓመት የ2ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን በመገምገም ልዩ ልዩ ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡
ዘጋቢ፡- ደምስ አረጋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!