ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን በድል ያጠናቀቀችበት ታሪክ የማይረሳው ቀን – ጥር 13/1954 ዓ.ም

25

ባሕር ዳር: ጥር 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1957 እንደጀመሩት ከታሪክ ማህደር እንረዳለን፡፡ የመጀመሪያው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታውም በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ነበር የተካሄደው፡፡

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1962 ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጀች፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለፍጻሜ ደርሶ ግብጽን 4 ለ 2 በመርታት አሸናፊ ኾነ፡፡

የቡድኑ አምበልም ሉቺያኖ ቫሳሎ ዋንጫውን ከአፄ ኃይለሥላሴ እጅ ተቀበለ።

በመጀመሪያዎቹ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተሳታፊዎች የነበሩት ሦስቱ ሀገራት ብቻ ነበሩ፤ ቀስ በቀስም ሌሎች ሀገራት ውድድሩን መቀላቀል ጀመሩ።

https://www.facebook.com/AMECOSport?mibextid=mna8qTP8xvtPE1tK

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ከመጠንሰስ ጀምሮ ሦስት ጊዜ አዘጋጅታለች፡፡ አንድ ጊዜ ዋንጫውን በማንሳትም ታሪክ ሠርታለች፡፡ ይሁንና ከዓመት ዓመት እያሽቆለቆለ ያለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዛሬ ላይ የሚፅናናበት ነገር ቢኖር ብሔራዊ ቡድኑ በታሪክ የማይረሳውን ገድል ያስመዘገበበት 3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ብቻ ነው።

ይህ ታሪካዊ የአፍሪካ ዋንጫ ድል ልክ በዛሬዋ እለት ከ62 ዓመታት በፊት ጥር 13 ቀን 1954 ነበር የተመዘገበው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በሚቀጥሉት አስር ቀናት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው እርጥበት ያገኛሉ” ኢንስቲትዩቱ
Next articleየሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምሮች ለኢኮኖሚ ልማት እና እድገት የላቀ አበርክቶ እንዲኖራቸው የሚደረገው ጥረት ይቀጥላል ሲል የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አስታወቀ።