
ባሕር ዳር: ጥር 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የናይሮቢ የፍጥነት መንገድ በቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉስ በአጼ ከኃይለ ሥላሴ ስም ተሰይሟል፡፡
የኬንያ መንገድ እና ትራንስፖርት ሚኒስትር ኪፕቾምባ ሙርኮመን መንገዱን መርቀው ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት የፍጥነት መንገዱ ወደ ናይሮቢ ሲቲ ሴንተር መግባት የሚያስቸል መሆኑን ነው፡፡
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) እንዲመሰረት ከፍተኛ ሚና በተጫወቱት በአፄ ኃይለ ሥላሴ ስም የተሰየመው መንገድ የመጀመሪያው የናይሮቢ የፍጥነት መንገድ እቅድ አካል ነው ተብሎለታል፡፡
ላለፉት 6 ወራት በመገንባት ላይ እንደነበርም የመንገድ እና ትራንስፖርት ሚኒስትሩ መግለጻቸውን ኤንቲቪ ዘግቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!