“ነባር የእርሻ እርከኖችን ማጠናከር እና አዳዲስ እርከኖችን በመሥራት የተጎሳቆሉ ቦታዎችን መጠገን ይገባል” የደቡብ ወሎ ዞን

9

ባሕር ዳር: ጥር 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ የ2016 ዓ.ም የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በወረዳው 03 ቀበሌ ተካሂዷል።

በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው የእርሻ ላይ እርከን ማሳደግን ጨምሮ ሌሎች የተፋሰስ ሥራዎች እንደሚሠሩ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

የቀበሌው አርሶ አደሮች በተፋሰስ ሥራው ተጠቃሚ መኾናቸውን በመግለጽ ሥራውን በተቀመጠለት ጊዜ ለመጨረስ ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።

እንደ ወረዳ የተፋሰስ ሥራውን በሁሉም 35 ቀበሌዎች በተቀመጠለት ጊዜ ሰሌዳ ለማጠናቀቅ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ቀድመው እንዳለቁ የገለጹት የቃሉ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አወል መሐመድ ናቸው።

የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ አህመድ ጋሎ በ2016 በጀት ዓመት በተፈጥሮ ሃብት ሥራው በተለይ የእርከን ማሳደግን ጨምሮ ለሌሎች የተፈሰስ ሥራዎች ቅድሚያ በመስጠት እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

ኀላፊው “ነባር የእርሻ እርከኖችን ማጠናከር እና አዳዲስ እርከኖችን በመሥራት የተጎሳቆሉ ቦታዎችን መጠገን ይገባል” ነው ያሉት፡፡

በቃሉ ወረዳ አሥተዳደር ሕዝቡን እና የሥራ ኀላፊዎችን በማስተባበር የተፈጥሮ ሃብት ሥራው በሁሉም ቀበሌዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚካሄድ ነው የተገለጸው።

ዘጋቢ፡- ደምስ አረጋ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር የተጠናከረ የዲፕሎማሲ ሥራ ይጠበቃል” አቶ ደመቀ መኮንን
Next articleኬንያ በኢትዮጵያ መሪ ስም የሰየመችው መንገድ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።