“ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር የተጠናከረ የዲፕሎማሲ ሥራ ይጠበቃል” አቶ ደመቀ መኮንን

11

ባሕር ዳር: ጥር 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር እና የተሳሳቱ ትርክቶችን ለማስተካከል የላቀ ዲፕሎማሲ አፈፃፃም እንሚጠበቅ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አስታወቁ።

ሰባተኛውን ቀን በያዘው የዲፕሎማሲ ሳምንት አካል የሆነው ዓመታዊው የሚሲዮን መሪዎች ስብሰባ ዛሬም ቀጥሏል።

በዚሁ መድረክ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባደረጉት ገለፃ በያዝነው 2016 በጀት ዓመት ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር፣ ወዳጅ ለማብዛት፣ የተደናገረውን ለማቅረብ፣ የላቀ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በአብሮነት፣ ዘላቂ እና የጋራ ልማት እንዲሁም ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ከሁሉም ሀገሮች ጋር ተደጋግፋ እንደምትሠራም ተናግረዋል። ለዚህም በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ፣ አህጉራዊ እንዲሁም የባለ-ብዙ ወገን የዲፕሎማሲ መስኮች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባም ገልፀዋል።

አቶ ደመቀ በስዊዘርላንድ ዳቮስ ላይ ሲካሄድ በቆየው የዓለም አቀፉ የምጣኔ ሀብት ጉባኤ (World Economic Forum) ላይ ተሳትፈው ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል ሲል ኢፕድ አስነብቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበክልሉ ያሉ ሃብቶችን ለመጠቀም የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መኾኑን የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ አሰታወቀ፡፡
Next article“ነባር የእርሻ እርከኖችን ማጠናከር እና አዳዲስ እርከኖችን በመሥራት የተጎሳቆሉ ቦታዎችን መጠገን ይገባል” የደቡብ ወሎ ዞን