በደብረ ብርሃን ከተማ የቃና ዘገሊላ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።

10

ባሕር ዳር: ጥር 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ጥር 12 ቀን የሚታሰበው የቃና ዘገሊላ በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በከተራ በዓሉ ላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የሰሜን ሸዋ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስና ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች፣ የየአድባራቱ አሥተዳዳሪዎች፣ ካህናት፣ የሰንብት ትምህርት ቤት መዘምራንና ምዕመናን ተገኝተዋል፡፡

በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ በገሊላ አውራጃ ቃና በሚባል ቦታ በተዘጋጀ የሰርግ ሥነ ሥርዓት ላይ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እና ደቀ መዛሙርቱ ጋር በመገኘት የመጀመሪያ ተአምሩን የገለጸበት መኾኑን የሃይማኖቱ አባቶች በትምህርተ ወንጌሉ ገልጸዋል።

ታቦተ ሕጉ ወደ ቤተ መቅደሱ ለመንቀሳቀስ ትንሽ ደቂቃዎች ቀርተውታል፤ በዓሉ በሰላም እየተከበረ እንደሚገኝም ከደብረ ብርሃን ከተማ መንግሥት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየቃና ዘገሊላ በዓል በኮምቦልቻ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።
Next articleየቃና ዘገሊላ በዓል በደሴ ከተማ በሁሉም አከባቢዎች ያለምንም ችግር የዕምነቱ አስተምህሮት በሚፈቅደው መሠረት እየተከበረ ነው።