
ባሕር ዳር: ጥር 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ጥር 12 ቀን የሚከበረው የቃና ዘገሊላ በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ ላይ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች፣ የየአድባራቱ አሥተዳዳሪዎች፣ ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንና ምዕመናን ተገኝተዋል፡፡
የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ወደ ቤተ-መቅደሱ እጅግ ባማረ ሃይማኖታዊ ሥነ – ሥርዓት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። በዓሉም በሰላምና በድምቀት እየተከበረ እንደሚገኝ ከከተማ አሥተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!