
ደሴ: ጥር 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ሕዝበ ክርስቲያኑ ጠዋት በኮምቦልቻ ከተማ ኳስ ሜዳ በመገኘት ሥርዓተ ጥምቀቱን ፈጽሟል።
ከእረፋድ ጀምሮ ደግሞ ከስድስቱም ደብር የተሰባሰበው ምእመን ታቦታቱን ወደ መንበራቸው በክብር በመሸኘት ላይ ይገኛል።
ቀሳውስት በጸሎት እና የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪወች ልዩ ልዩ መንፈሳዊ መዝሙሮችን እያሰሙ ነው።
ወጣቶች ታቦታት የሚያልፉባቸውን ጎዳናዎች በማፅዳት እና ምንጣፍ በመሸከም በዓሉን በልዩ ድባብ እያደመቀት ነው።
ዘጋቢ፦ አበሻ አንለይ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!