በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ከተማ የጥምቀት በዓል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው።

39

ባሕር ዳር: ጥር 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በበዓሉ በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤቴክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የምዕራብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሰላማና የምዕራብ ጎንደር ዞን ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አባተ ነጋን ጨምሮ ሌሎች ሕዝበ ክርስቲያን፣ የበዓሉ ታዳሚ ምዕመናን እና እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤቴክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የምዕራብ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሰላማ የጥምቀት በዓል በዓለምአቀፍ የባሕል፣ የትምህርትና የሳይንስ ምርምር ተቋም (ዩኔስኮ) የተመዘገበና ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ መኾኑን ገልጸዋል።

ብጹዕነታቸው የጥምቀት በዓል ለኦርቶዶክሳያዊያን ከአምላካችን ትህትናን፣ ፍቅርን፣ አንድነትንና ድኅነትን ተጎናጽፈን ዘላለማዊ ፍቅርን ያገኘንበት በዓል በመኾኑ ለሰላምና ለፍቅር ይቅር ተባባሉ ብለዋል ለምዕመናኑ።

ካህናቱ ፣ ሕዝበ-ክርስቲያኑና ሌሎች ታዳሚዎች በዓሉን በሚያደምቁ የተለያዩ አልባሳት አሸብርቀው በባሕረ ጥምቀቱ የጸበል ርጭት በረከት ለምዕመናኑና ለበዓሉ ታዳሚዎች እየተሰጠ ይገኛል።

የጥመቀት በዓሉ ካለፉት ዓመታት በተሻለና በደማቅ ሁኔታ ሃይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ እየተከበረ ነው።

ምንጭ:- የምዕራብ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጥምቀት በዓል በእንጅባራ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ነው።
Next articleየጥምቀት በዓል በደብረታቦር ከተማ እየተከበረ ነው።