“ክርስቶስ በጥምቀቱ የሰጠንን ሰላም እኛ ልንጠብቀው ይገባል” የሰቆጣ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ መላሽ ወርቃለም

8

ሰቆጣ: ጥር 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰቆጣ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው የጥምቀተ በዓል የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ መላሽ ወርቃለም ክርስቶስ በጥምቀቱ የሰጠንን ሰላም እኛ ልንጠብቀው ይገባል ብለዋል።

የዛሬውን የጥምቀት በዓል ስናከብር በዞናችን ያሉ የተቸገሩ ወገኖችን በማሠብና በመደገፍ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።

ከንቲባው ኢየሱስ ክርስቶስም በዮርዳኖስ ወንዝ ሲጠመቅ ነጻነትን፣ ሰላምን፣ መከባበርንና ትህትናን አሳይቶናል ብለዋል።

ለእምነቱ ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ በማለትም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው መልእክት አስተላልፈዋል።

በአሁኑ ሰዓትም የጥምቀቱ ሥርዓት እየተከናወነ ይገኛል። ብጹዕ አቡነ በርናባስና አቨው ካህናትም ሕዝቡን እያጠመቁ ይገኛሉ።

በደጀን ታምሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጥምቀትን በዓል ስናከብር የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በማብሰር እና ሰላምን በመስበክ መኾን ይገባል” ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ
Next article“ባሕር ሸሸች፤ ዓለም በብርሃን ተመላች”