
አዲስ አበባ: ጥር 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እየተከበረ ነው።
በበዓሉ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስን ጨምሮ የሃይማኖቱ አባቶች እና አማኙ በተገኙበት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች ነው እየተከበረ የሚገኘው።
ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብረሃነ ኢየሱስ “የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በማሰብ ሀገራችን ሰላም እንድትኾን በመፀለይ እና በመትጋት ልናከብር ይገባል” ብለዋል።
ሊቀ ጳጳሱ “የጥምቀትን በዓል ስናከብር የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በማብሰር እና ሰላምን በመስበክ መኾን ይገባል” ነው ያሉት
ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረን አስተምህሮ መተባበር፣ መረዳዳት እና አንድነት ነው ይህንን ልንተገብር ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉዑሽ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!