
ባሕር ዳር: ጥር 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ በተለምዶ ዲፖ ተብሎ በሚጠራው ጥምቀተ ባሕር ሥርዓተ ጥምቀቱ በካህናት ተጀምሯል።
የጥምቀት በዓል የሚከበረው ኢየሱስ ክርስቶ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወርዶ በፍጡሩ እጅ በእደ ዮሐንስ መጠመቁን በማሰብ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት የአዳም የእዳ ደብዳቤ ተደምስሶ የሰውን ልጅ ከባርነት ነፃ ያወጣበት ቀን በመኾኑ በክርስቲያኖች ዘንድ የመዳን በዓል ኾኖ ይከበራል።
ከኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትም ምእመናን ፍቅርን፣ ትህትናን፣ አንድነትን እና መተሳሰብን ሊማሩ እንደሚገባ የጥምቀቱ አስተምህሮ ይነግረናል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!