
ባሕር ዳር: ጥር 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ በባሕረ ዮርዳኖስ መጠመቁን ተከትሎ በባሕረ ጥምቀቱ ሃይማኖታዊ ሥርዓት በሰቆጣ ከተማ እየተከበረ ነው።
በባሕረ ጥምቀቱም የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ በርናባስ፣ አበው ሊቃውንት፣ የከተማው ከንቲባ መላሽ ወርቃለም፣ አፈ ጉባኤ ፈንታይቱ ካሤን ጨምሮ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ዲያቆናት እና የሰንበት ተማሪዎች እንዲሁም የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።
የባሕረ ጥምቀቱ ሥርዓተ ቅዳሴም እየተከናወነ ይገኛል።
ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!