የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በባሕር ዳር ከተማ ዓባይ ማዶ ጥምቀተ ባሕር በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እየተከበረ ነው።

7

ባሕር ዳር: ጥር 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በበዓሉ ላይ የተገኙት የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የጥምቀት በዓል ፈጣሪ ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር ካሳየበት መካከል አንዱ ነው ብለዋል።

እኛም የክርስቶስን አርዕያነት በመከተል ሀገራችን መውደድ፣ ይቅር መባባል እና በፍቅር መኖር እንደሚገባ ገልጸዋል።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ሰው ከፈጣሪ ይቅርታ ለማግኘት ለወዳጆቹ ይቅርታ ማድረግ ይገባዋል ብለዋል። አሁን ላይ የሚስተዋለው ልዩነት እና ግጭት ከኢየሱስ ክርስቶስ አርእያነት ያፈነገጠ ስለኾነ ወደ ቀደመው መዋደድ፣ መከባበር እና ይቅር መባባላችን መመለስ አለብን ብለዋል።

በዓሉ የቱሪስት መስህብ እና ገጽታ መገንቢያም ስለኾነ ከሀገር ውስጥም ከውጪም የሚመጡ እንግዶችን በተለመደው የእንግዳ አክባሪነት ባህል ልናስተናግድ ይገባል ብለዋል።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በዓሉ ሥርዓቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከናወን እየሠሩ ለሚገኙ ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የጸጥታ ኃይሎች ምስጋና አቅርበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጽድቅ እውነት ነው፤ በተግባር ልንፈጽመው ይገባል” ብጹዕ አቡነ አብርሃም
Next articleየባሕረ ጥምቀቱ በዓል በሰቆጣ ከተማ እየተከበረ ነው።