“ጽድቅ እውነት ነው፤ በተግባር ልንፈጽመው ይገባል” ብጹዕ አቡነ አብርሃም

17

ባሕር ዳር: ጥር 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በባሕር ዳር ከተማ የዓባይ ማዶ ጥምቀተ ባሕር የጥምቀት ሥነ ሥርዓት በሃይማኖቱ ሥርዓት ቀጥሏል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ አብርሃም ለምዕመኑ ሃይማኖታዊ ትምህርት እና ቡራኬ ሰጥተዋል።

“ጽድቅ እውነት ነው፤ በተግባር ልንፈጽመው ይገባል” ያሉት ብጹዕ አቡነ አብርሃም በዘመናችን ትውልዱ ከእውነት እየራቀ ነው ብለዋል። ብጹዕነታቸው ሰላም እንዲኖር እውነትን መስበክና መሥራት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል። ከእውነት የራቀ ትውልድ በግጭት እና በጦርነት እየተሰቃየ እንደኾነ አመላክተዋል።

ብጹዕ አቡነ አብርሃም እውነትን እና ጽድቅን ለመፈጸም በፍቅር እና በሰላም መኖር አለብን። ችግሮችን ሁሉ በሰላም መፍታት ከሁሉም የሚጠበቅ ኀላፊነት ነው ብለዋል። መተዛዘን፣ መረዳዳት እና መታረቅ ዘመኑ የሚጠይቀን ክርስቲያናዊ ግብረ ገብነት ነውም ብለዋል።

በሥነ ሥርዓቱ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው፣ ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ፣ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መላዕከ ሰላም ኤፍሬም ሙሉዓለም እና የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መላዕከ ገነት አምደ ሃይማኖትን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች እና የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እየተሳተፉ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጥላቻን በፍቅር መለወጥ፣ በቀልን በይቅርታ ማሸነፍ፣ እና ግጭትን በእርቅ መዝጋት ይገባል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው
Next articleየኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በባሕር ዳር ከተማ ዓባይ ማዶ ጥምቀተ ባሕር በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እየተከበረ ነው።