
እንጅባራ: ጥር 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ትህትናን ለማስተማር ሲል በፍጡሩ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ ዝቅ ብሎ መጠመቁን አብነት በማድረግ በየዓመቱ በልዩ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት የሚከበረው የጥምቀት ዋዜማ የከተራ በዓል በእንጅባራ ከተማ በእምነቱ ተከታዮች በድምቀት በመከበር ላይ ነው።
በከተማዋ ከሚገኙ ከሁሉም አድባራት ታቦታት በሃይማኖት አባቶች፣ በሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራንና በምዕመናን ዝማሬና እልልታ ከመንበረ ክብራቸው ወርደው ወደተዘጋጀላቸው ጥምቀተ-ባህር በመሸኘት ላይ ናቸው።
በተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት የተደራጁ ወጣቶችም ታቦታት የሚያልፉባቸውን ጎዳናዎችና ባህረ ጥምቀቱን በማፅዳት፣ በማስዋብና በማስተባበር የበዓሉ ድምቀት ሆነዋል።
በሳሙኤል አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!