
ባሕር ዳር: ጥር 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በቀጣናዊ እና ሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በ19ኛው የገልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥታት ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ካምፓላ የገቡት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ከጉባዔው ጎን ለጎን ተገናኝተው መክረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ከገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ጉባዔ ጎን ከፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ጋር ተገናኝተን በቀጣናዊ እና ሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል” ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!