
ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋ እንዲመለስ በሰላማዊ እና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ መስራቷን እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና የልዑካን ቡድናቸው በኡጋንዳ ካምፓላ እየተካሄደ በሚገኘው የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥታት 19ኛው ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የሕዝቦቻቸውን የልማት ፍላጎት ለማሟላት እየተቸገሩ መኾናቸውን እና ከባድ ፈተናዎች እንደሚገጥማቸው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያም ይህን ችግር ለመፍታት በሰላማዊና በጋራ ተጠቃሚነት እንዲሁም በድርድር መፍትሄ ለማግኘት ጥረት እያደረገች መኾኑን ማስረዳታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ገልጸዋል።
ባሕር ዳር: ጥር 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!