
ባሕር ዳር፡ ጥር 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክርቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ ለከተራና ጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
የጥምቀት በዓል በመላው ሀገራችን በጉጉት የሚጠበቅ በአደባባይ የሚከበር ሃይማኖታዊ ሥርዓቱንና ትዉፊቱን ጠብቆ ለዘመናት ሲከበር የመጣ ነው። ለቱሪዝም ኢንዱስትሪው ዘርፍ ዕድገት ያበረከተዉ አሰተዋጽኦ እና ጠቀሜታም እጅግ ከፍተኛ ነው።
ስለዚህ በዓሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱንና ትውፊቱን ጠብቆ በሰላምና በድምቀት እንዲከበር ማድረግ የሁላችንም ኃላፊነት መሆኑን ተገንዝበን ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በኃላፊነት መንፈስ መልካም አስተዋፅዖ በማበርከት፤ አብሮነታችንን በማጠናከር እና በመተጋገዝ መከበር ይኖርበታል፡፡
በድጋሜ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ!
መልካም በዓል
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!