የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በደሴ ከተማ ታቦታት የሚያልፍበትን መንገድ አጸዱ።

11

ባሕር ዳር: ጥር 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በደሴ ከተማ ታቦታት የሚያልፍበትን መንገድ አጽድተዋል፡፡

በሥፍራው የሚገኘው ሬጅመንት ዋና አዛዥ የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ሠራዊቱ የመዝገበ ምህረት ቅድስት ማርያም ታቦት የሚወጣበትን መንገድ ከማኅበረሰቡ ጋር በጋራ ማጽዳቱን አንስተዋል፡፡

“እኛ ከሕዝብ እንደወጣን ሁሉ የሕዝብ በዓላትን የመጠበቅ ግዴታ አለብን” ማለታቸውንም የከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ዋና አዛዡ የመከላከያ ሠራዊት ከኅብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያ የተውጣጣ እና የሕዝብ ልጅ ስለሆነ ሕዝቡ ከመከላከያ ጎን ሊተባበር ይገባል ብለዋል።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮችም ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና የልዑካን ቡድናቸው ዑጋንዳ ካምፓላ ገቡ።