“በክልሉ የተፈጠረውን ቀውስ ወደ ቀደመ ሰላም ለመመለስ የፀጥታ ኃይሉን አቅም በሥልጠና የመገንባት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል” የአማራ ክልል ሰላም እና ደኅንነት ቢሮ

22

ደብረ ማርቆስ: ጥር 9/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በደብረ ማርቆስ ከተማ ክልላዊ፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን መረዳት የሚያስችል ሥልጠና ለፀጥታ መዋቅሩ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ቀጣይነት ያለው የአጭር እና የረዥም ጊዜ ሥልጠናን ማጠናከር ትኩረት እንደሚሰጠው በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የክልሉ ሰላም እና ደኅንነት ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው ገልጸዋል፡፡

ሥልጠናውን የወሰዱ የፀጥታ ኃይል አመራሮች እና ፈጻሚ አካላት ሥልጠናውን ገቢራዊ ማድረግ እንዳለባቸውም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በሥልጠና ሂደቱ ላይ የተገኙት የጎጃም ቀጣና ኮማንድ ፖሰት አባል፣ የምዕራብ እዝ ምክትል አዛዥ እና የቀጣናው ሎጅስቲክስ አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ሙላት ጀልዱ ጠንካራ የፀጥታ መዋቅር መፍጠር እና ማደራጀት አስፈላጊ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

ክፍተቶችን ማረም እና ማስተካከል እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) የሥልጠናው ዋና ዓላማ የሕዝቡን ሰላም ማስጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ የፀጥታ መዋቅር እና ተቋም መፍጠር መኾኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት ያጋጠሙትን ችግሮች ነቅሶ ለማውጣት፣ ለማረም እና ለማስተካከል ሥልጠናው የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡ በሥልጠናው እየተሳተፉ ያሉ አመራሮች የሕዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ እንዲሁም በተሳሳተ እና በተዛባ አመለካከት ከመዋቅሩ ውጭ ያሉ አካላትን ለመመለስ እና ለማስተካከል እንደሚሠሩም ተናግረዋል፡:

ዘጋቢ፡- የኔነህ አለሙ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሕዝበ ክርስቲያኑ በዓለ ጥምቀቱን ሲያከብር ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሊኾን ይገባል” የባህር ዳር ሀገረ ስብከት
Next articleባሕላዊ አልባሳት የጎንደር ጥምቀት ሌላ ድምቀቶች!