አቶ ደመቀ መኮንን ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን መስራች እና ሊቀ መንበር ቢል ጌትስ ጋር ተወያዩ።

50

ባሕር ዳር: ጥር 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ መስራች እና ሊቀ መንበር ቢል ጌትስ ጋር ዛሬ ተወያይዋል።

ውይይቱን ያደረጉት በስዊዘርላድ ዳቮስ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ነው። በዚህም ወቅት ቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በጤና፣ በግብርና እና በሰው ሃብት ልማት በኢትዮጵያ እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ አቶ ደመቀ ምሥጋና አቅርበዋል።

የምጣኔ ሃብት እድገትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ መንግሥት ለሚያደርገው ጥረት ፋውንዴሽኑ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ ደመቀ ጠይቀዋል። የቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን መስራች እና ሊቀ መንበር ቢል ጌትስ ፋውንዴሽኑ የዜጎችን ሕይወት ለመለወጥ የሚያስችሉ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ መሥራት እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ፋውንዴሽኑ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ገደማ መንግሥት ቅድሚያ በሚሰጣቸው የልማት ዘርፎች የሰዎችን ኑሮ የለወጡ ሥራዎችን በኢትዮጵያ በማከናወን ተጠቃሽ አስተዋፅኦን በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleናኦሚ ግርማ የአሜሪካ የ2023 የምርጥ ተጫዋቾችን ሽልማት አሸነፈች፡፡
Next article“ሕዝበ ክርስቲያኑ በዓለ ጥምቀቱን ሲያከብር ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሊኾን ይገባል” የባህር ዳር ሀገረ ስብከት