ትምህርት ሚኒስቴር በድጋሚ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና መርሐ ግብር ይፋ አደረገ፡፡

58

ባሕር ዳር: ጥር 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ትምህርት ሚኒስቴር ከ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም ቅድመ ምረቃ መርሐ ግብሮች ላይ ለእጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና እየሰጠ ነው፡፡

በ2016 አጋማሽ ዓመት ላይ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ ለሚጠባበቁ ተፈታኞች የፈተና መርሐ ግብሩን ይፋ አድርጓል፡፡

ሐምሌ/2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን ወስደው ያላለፉ እና በድጋሚ ፈተናውን ለመውሰድ ለሚጠባበቁ ተፈታኞች የፈተናው መርሐ ግብር ከጥር 27/2016 ዓ.ም እስከ የካቲት 1/2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ በማኅበራዊ የትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለተፈታኝ ተማሪዎች ባወጣው ማስታወቂያ ላይ እንዳስታወቀው በድጋሚ ለሚፈተኑ እጩ ተመራቂዎች የምዝገባ መርሐ ግብሩ ከጥር 8/2016 ዓ.ም እስከ ጥር 15/2016 ዓ.ም 500 ብር በቴሌ ብር በመክፈል ብቻ እንደሚፈጸም አስታውቋል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ የሚመዘገቡ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚያካሂዱት እና ክፍያ የሚፈጽሙት በትምህርት ተቋማቸው በኩል መኾኑንም አስታውቋል፡፡

ተፈታኞች ተጨማሪ መረጃ እና ድጋፍ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር +251 118 13 21 76 ወይም በኢሜይል registration@ethernet.edu.et በኩል ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉ ያስታወቀው ሚኒስቴሩ ድጋሚ ተፈታኞች ምዝገባ የሚያካሂዱት እና የመፈተኛ የመንግሥት ተቋም የሚመርጡት https://exam.ethernet.edu.et ሊንክ ላይ መኾኑን ጠቁሟል፡፡

በታዘብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ ተናፋቂውን ጥምቀት፤ በታሪካዊቷ እመቤት”
Next article“በተፈጥሮ ሃብት ልማት በዚህ ዓመት የተሻለ ውጤት ለማግኘት እየሠራን ነው” የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር